አብዛኛዎቹ የሚዲያ ተቋማት የስርዓተ – ጾታ ፖሊሲ የላቸውም፡፡

By emwa — In News — October 30, 2023

30

Oct
2023

አዲስ አበባ ጥቅምት 13፣ 2016 ዓ.ም ማህበራችን ከ ፎጆ አይ ኤም ኤስ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ባስጠናው ጥናት አብዛኛዎቹ የሚዲያ ተቋማት የ ስርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንደሌላቸው አረጋገጠ፡፡

በዚህም ማህበራችን ያከናወነውን የመነሻ ግምገማ ለ የሚዲያ ተቋማት እና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት በስርዓተ ፆታ ፖሊሲ እና አተገባበር ዙሪያ ያከናወነውን ጥናት አቅርቧል፡፡

የጥናቱ አላማ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን የስርዓተ ፆታ ፖሊሲ ህልውናን ለማወቅ እና ክፍተቶችን በመለየት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ዘዴዎችን ማቅረብ ነው በዚህም ጥናቱ ከተካሄደባቸው 18 ብሮድካስት እና ኦንላይን የሚዲያ ተቋማት የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ብቻ ፖሊሲው እንዳለው የገለፀ ሲሆን ቀሪዎች የሚዲያ ተቋማት እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

በቀጣይም ኢትመባሴማ  ይህንን የመነሻ ግምገማ ጥናት መሰረት በማድረግ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች 7 የክልል ከተሞች ሚዲያ ተቋማት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የስርዓተ ፆታ አስፈላጊነት እና አተገባበሩ ዙሪያ ስልጠና ይሰጣል፡፡