የስራቴጂክ እቅድ አዘገጃጀት ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

By emwa — In News — October 14, 2023

14

Oct
2023

አዲስ አበባ ጥቅምት 3፣ 2016 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሴቶች ማህበር (ኢትመባሴማ) ከ ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የስራቴጂክ እቅድ አዘገጃጀት ላይ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

የምክክር መድረኩ የተካሄደው ኢትመባሴማ ለሚያዘጋጀው የ 5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ሲሆን ፤ የስትራቴጂክ እቅዱ ኢትመባሴማ ለቀጣዩ አምስት አመታት የሚጓዝበትን አቅጣጫ ለመግለፅ እና ከታቀደለት ራዕይ እና ተልዕኮ ጋር የሚጣጣሙ ተጨባጭ ዓላማዎችን እና ግቦችን ለማቋቋም የሚረዳ ስልታዊ እቅድ ነው።

በዚህ የምክክር መድረክ ከቦርድ አባላትና እንዲሁም ከማህበሩ አባላት ግብዓት የተሰበሰበ ሲሆን በዚህም ኢትመባሴማ እስከዛሬ የነበረውን የስራ አፈፃፀም ፣ የሒሳብ ዘገባ እና የአመራርነት ይዘት ዘገባዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡