ለአባላት ስልጠና ተሰጠ

By emwa In News

03

Jan
2024

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሴቶች ማህበር ከ ኢንተርኒውስ ጋር በመተባበር ለ ጋዜጠኞች ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናው ለአራት ተከታታይ ቀናት ከ ታህሳስ 16 እስከ ታህሳስ 19፣ 2016 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን በዋናነት ስርዓተ-ጾታን አገናዛቢና አካታች የግጭት ዜና አዘጋገብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡  

በዚህም ከአማራ፣ ከኦሮሚያ እና ከትግራይ እንዲሁም ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሴት ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ ጋዜጠኞች የግጭት ጉዳይ እና የ ስርዓተ ፆታ መረጃ ሲሰሩ ሊተገብሩ የሚገቧቸውን መረጃዎች ለማስተላለፍ ሲሆን በዚህም የግጭት ጉዳይ ሲዘገብ እንዴት ገለልተኛ መሆን እንደሚቻል እንዲሁም በእያንዳንዱ ዜና ላይ ዜናው ምን ያህል የስርአተ ፆታ ፖሊሲን ያካተተ መሆን እንዳለበት መገንዘብ እንደሚገባ በዋናነት ትኩረት የተሰጠበት ክፍል ነው ፡፡

በመጨረሻም ጋዜጠኞቹ የተሰጣቸውን ስልጠና በየመስራቤታቸው ለመተግበር እንዳቀዱ ገልጸዋል፡፡