በተለያዩ የሃገሪቱ  ክልሎች ሲሠጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

By emwa In News

02

Dec
2023

ህዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም 

ማህበራችን ከ ፎጆ አይ ኤም ኤስ ጋር በመተባበር በተለያዩ ክልሎች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና በአዲስ አበባ አጠናቀቀ፡፡

የስልጠናው መነሻ ማኅበራችን በመገነኛ ብዙሃን ተቋማት የስርዓተ ፆታ ፖሊሲ ህልውና  እና አተገባበር ዙሪያ ያጠናውን ጥናት ተመርኩዞ ሲሆን በተደረገው ጥናት አብዛኛዎቹ የሚዲያ ተቋማት የስርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንደሌላቸው በማረጋገጡ ነው፡፡

ስልጠናው የተሰጠው ለመገናኛ ብዙሃን እና ለኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ሲሆን በስልጠናው የየተቋማቱ ዳሬክተሮች ፣ አርታኢዎች ፣ ፕሮግራም አዘጋጆች እና ሪፖርተሮች ተሳትፈዋል፡፡

በዚህም አዲስ አበባን ጨምሮ በ አስር የክልል ከተሞች 160 ጋዜጠኞች እና የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠናውን ወስደዋል፡፡

በዚህም ስልጠና የጾታ እና የስርዓተ ፆታ ጽንሰ-ሀሳብ ፣የሥርዓተ-ፆታ ባህሪያት ውጤቶች እና ደንቦች ፣ ሴቶችን የማብቃት አካሄድ እና የስርዓተ ጾታ ፖሊሲን እንዴት መተግበር እንደሚቻል በሚገባ ተብራርቷል፡፡

ማህበራችን ይህንን ስልጠና ለጋዜጠኞችና ኮሚዩኒኬሽን ባሙያዎች ሲሠጥ በቀጣይ ሰልጣኞች በየተቋማቸው የስርዓተ ፆታ ፖሊሲ እንዲያዘጋጅ መንገድ ይከፍታሉ ብሎ በማመን ነው፡፡